ላይ
/lay/መስተዋድድ
ትርጉሞች
በመቆሚያ፣ በመኖሪያ ላይ በሚነገር፤ በምድር ላይ፣ በአካል ላይ፣ በሁኔታ ላይ ሲነገር፤
ምሳሌዎች
ለምሳሌ ወረቀቱ በጠረጴዛው ላይ ነው ይባላል)። መኖሪያን፣ መቆሚያን ቦታን ለቆ ከምድር በላይ በአየር ሲያንዣብብ ከምድር በላይ ይሆናል። በረቀቀ ነገር ላይ የሚነገር፤ በእጅ የማይዳሰስ የነገር ሀሳብ ቦታ ሲሆን ገና በሀሳብ ላይ ነው ይባላል። በቦታና በአካል ላይ የሚገዛ የንግግር መሰረት ነገር ሁሉ በአግባብ ላይ የሚመሰረት ስለሆነ በሰማይ ላይ፣ በምድር ላይ ይባላል። ስልጣን፣ ማዕረግ ከእከሌ በላይ ሆኖ ተሾመ ሲባል፤ የበላይነት የተባለው በሁለት ሰዎች መካከል ገብቶ ያንዱን የበላይነት የሁለተኛውን የበታችነት የሚያሳይ ነው...(የቀጠለ) ሲባል የበላይነት የተባለው በሁለት ሰዎች መካከል ገብቶ ያንዱን የበላይነት የሁለተኛውን የበታችነት ለይቶ ያሳያል። «ላይ ላይ ላዩን መሄድ» — ወደ ውስጥ አለመግባት፤ ላይ በላይ መንሳፈፍ፤ አለመዘቀጥ፤ አለመጥለቅ። አንድን ነገር አስመልክቶ ለመናገር ወይም አቅጣጫን፣ አንፃርን፣ አያያዝን ለመጥቀስ የሚያገለግል (ለምሳሌ፦ «በእሱ ላይ እምነት የለኝም»)። አንድ ነገር ከስንት ቦታ እንደተከፈለ የሚያሳይ (ለምሳሌ፦ «እንጀራውን ባርኮ አምስት ላይ ከፈለው»)።
አስተያየቶች
በመጫን ላይ...
አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።